ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪ እና አካታች የሳይንስ ሥነ-ምህዳር። በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ በኩል ከድህነት ወጥመድ እና ከመካከለኛ ገቢ ወጥመድ ለመላቀቅ የሚያስችል መንገድ።
በ2030 በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት ተወዳዳሪና ተመራጭ ሀገር ሆና ማየት ፡፡
ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ምቹ ሥነ-ምህዳር በመፍጠር፤ ዘርፉ ለሥራ ዕድል እና ለሀብት ፈጠራ እንዲሁም ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ዕድገት ያለውን ድርሻ ማሳደግ ነው፡፡
1) ፍላጎትን መሰረት ያደረገ እና የቀጣይ ዘመን ኢንዱስትሪ ውስጥ በብቃት የሚሳተፍ የሰው ኃይል የሚፈጠርበትን ሥርዓት መዘርጋት፤
2) ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር፣ እንዲሁም ለኢኖቬሽን መደላድል ለመፍጠር የሚያስችል መሰረተ-ልማቶችን በቀጣይነት ማልማት፤
3) ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ቢዝነስን መሠረት ያደረጉ ኢኖቬሽኖችን በማበረታታት ለስራ ዕድል፣ ለሀብት ፈጠራና ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ዕድገት ድርሻ ማሳደግ፤
4) በቴክኖሎጂ ልማትና ኢኖቬሽን የግሉን ዘርፍ ሚና በማሳደግ መሪነቱን ማረጋገጥ፤
5) የሀገር በቀል ዕውቀቶችን በማልማት ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችል የአደረጃጀት እና የአሠራር ሥርዓት በመፍጠር የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ባህል መገንባት፤
6) የተቋማት ትስስርና ትብብርን በማጠናከር ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለምአቀፋዊ አጋርነት እና ተጠቃሚነትን ማሳደግ፤
7) ምቹ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሥነ-ምህዳር እንዲፈጠር የሚያስችሉ የሕግና የአሠራር ማዕቀፎችን መዘርጋት፤
ከዋናው የፖሊሲ ሰነድ የተገኘ ትክክለኛ ጽሑፍ
ከርዕይ አኳያ፡- የSTI ፖሊሲ ርዕዩ በ2030 ተደርጎ ይገለጽ እንጂ ከሀገራችን የ2023 ዓ.ም ሆነ የ2040 ዓ.ም ራዕይ ጋር የተሰናሰነ ነው። Not only from poverty trap but also from middle income trap.
ከዘርፍ አኳያ፡- በኢኖቬሽንና ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነት ስር ግብ-1(6) “የዲጂታል መሰረተ-ልማትና አስቻይ ሥርዓቶችን በመዘርጋት የዲጂታል ኢኮኖሚ ይገነባል” ከማለቱ ውጭ Specifically የተጠቀሰ ዘርፍ የለም።
ከቴክኖሎጂ አኳያ፡- በአካባቢያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ልማት ስር በግብ-2 ከቁጥጥር ጋር ተያይዞ የጨረራ፣ የኒውክላር፣ የኬሚካል እና የሥነ-ህይወት ቴክኖሎጂ ከመጠቀሱ ውጭ Specifically የተጠቀሰ ቴክኖሎጂ የለም። (short cycle / long cycle / disruptive)
አዳዲስ እውቀት ማመንጨት (Nat'l security, Nat'l pride). መሳሪያዎች፡ Public research funds, Tax incentives, Higher Education, Research Institutions, IPRs.
ትኩረቱ ቴክኒካዊ እውቀትን ጥቅም ላይ ማዋል እና ማዘመን። መሳሪያዎች፡ Public procurement, aid to strategic sectors, training, standardization, forecasting, benchmarking.
የአጠቃላይ ኢኮኖሚውን innovative performance ማሳደግ ላይ ያተኮረ። ✓ የተቋማትን የአሠራር ሥርዓት ማዘመን፤ ✓ የመረጃ ተደራሽነት ማሳደግ፤ ✓ የቁጥጥር ስራዎች (Environmental, Bioethical)፤ ✓ የሸማቾች ጥበቃና ፍትሐዊ የንግድ ውድድር፤ ✓ ክላስተሮች እና የኢንዱስትሪ ዞኖች ማስፋፋት፤ ✓ ጥልቅ የተሞክሮ ቅመራ እና ትንበያ (including trade secret).
R&D funding, feed-in-tariffs, subsidy schemes, tax incentives for R&D and technology adopters.
Environment, standardization, IPRs, competition law, bankruptcy law, public procurement, support to private demand.
Education & training, business advisory, market intelligence, awareness raising.
Clusters, industry zones, S&T Parks, trade tariffs, regional innovation networks.
በፖሊሲው መርሕ ቁ/1፡ የግሉ ዘርፍ በሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ልማትና ትግበራ ውስጥ መሪ እንዲሆን ይደረጋል።
በፖሊሲው ዓላማ ቁ/4፡ በቴክኖሎጂ ልማትና ኢኖቬሽን የግሉን ዘርፍ ሚና በማሳደግ መሪነቱን ማረጋገጥ።
የፖሊሲው ተልዕኮ፡ ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ምቹ ሥነ-ምህዳር በመፍጠር፤ ዘርፉ ለሥራ ዕድል እና ለሀብት ፈጠራ እንዲሁም ለአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ዕድገት ያለውን ድርሻ ማሳደግ ነው።
ግብ-2(2): ለምርምርና ስርጸት በቂ በጀት ይመደባል። የታሪፍ፣ የታክስ ማበረታቻዎች፣ የሪስክ ካፒታል ሥርዓት፣ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ።
ግብ-4(3): የሀገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀምና ለማሳደግ ሥርዓት። ግብ-2(1): ማዕከላዊ አክሬዲትድ ላብራቶሪዎች። ግብ-2(2): የምርምር መሰረተ-ልማት ማጠናከር።
ግብ-3(2): የላቀ እውቀትና ክህሎት ያላቸው ቴክኒሺያኖችን ማፍራት። ግብ-1(4): ምቹ የምርምር ሥነ-ምህዳር። ግብ-1(3): የግል-መንግስት አጋርነት።
ግብ-2(4): በአካባቢና በሰው ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ቴክኖሎጂዎች የአጠቃቀምና አወጋገድ ሥርዓት። የሀብት አመዳደብ ውጤታማ፣ ተጠያቂ እና ግልጽ መሆን አለበት።
የዜጎች ደህንነት የስኬት መለኪያ፣ የሥራ እድል ፈጠራ፣ የዕድሜ ልክ ትምህርት፣ ልዩ ተሰጥዎ ላላቸው ድጋፍ።
ሴቶች፣ ወጣቶች እና ተጋላጭ ክፍሎች ተሳታፊ እንዲሆኑ፣ ተደራሽ ፋይናንስ እና ፍትሐዊ የልማት አሰራር። በፖሊሲው ትግበራ ሂደት አካታችነት ይረጋገጣል።
በዘርፍ አለመገደብ፣ ለሁሉም ቴክኖሎጂዎች ክፍትነት፣ ተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ማስተናገድ፣ በቁጥር ያልተገደበ የኢንቨስትመንት ጥምርታ።
| ተ.ቁ. | ወሳኝ የፖሊሲ ጉዳዮች | ግቦች | የአፈፃፀም ስልት (Goal References) |
|---|---|---|---|
| 1 | የሰው ሃብት ልማት | 4 | ግብ-1(2)፤ ግብ-2(2)፤ ግብ-3(4)፤ ግብ-4(4) |
| 2 | የቴክኖሎጂ ልማት፣ ሽግግር እና የእውቀት አስተዳደር | 4 | ግብ-1(3)፤ ግብ-2(3)፤ ግብ-3(3)፤ ግብ-4(3) |
| 3 | ምርምርና ልማት | 3 | ግብ-1(5)፤ ግብ-2(4)፤ ግብ-3(2) |
| 4 | ኢኖቬሽን እና የኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪነት | 2 | ግብ-1(6)፤ ግብ-2(2) |
| 5 | የፋይናንስ አቅርቦት፣ መዋዕለ-ንዋይ፣ ድጋፍና ማበረታቻ | 3 | ግብ-1(2)፤ ግብ-2(3)፤ ግብ-3(2) |
| 6 | ጥራትና አእምሯዊ ንብረት | 4 | ግብ-1(3)፤ ግብ-2(2)፤ ግብ-3(2)፤ ግብ-4(3) |
| 7 | ትብብር እና ትስስር | 2 | ግብ-1(4)፤ ግብ-2(5) |
| 8 | አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ልማት | 2 | ግብ-1(4)፤ ግብ-2(4) |
የመንግስት ፍላጎት፡- Proclamations, regulations, guidelines, standards, programs, projects, detail implementation strategies.
Transversal Nature of STI Policy: National Policy Alignment / program alignment. Establishment of STI Councils (NIS, RIS, SIS, TIS) at Federal & Regional Government Level.
Return on Investment: pragmatic approach while choosing strategic technologies.
Institutional Capability: the policy is all about 3I (Innovation, Infrastructure, Institutional Interlinkages).
ማጣቀሻዎች፡ Home Grown Economy Digital.pdf · STI Policy Revision Study Review.pdf · SDG 2030/AU2063 · ብሔራዊ ራዕይ · የ10 ዓመት እቅድ (EPDC)